ምክር እና መመሪያ

የጥገኝነት ማመልከቻ አሰራር ውስብስብ እና ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ይገባናል። በየደረጃዎቹ ያሉትን አሰራር የሚያስረዳ መመሪያ አዘጋጅተናል። መብታችሁን እና ሓላፊነታችሁን ተረድታችሁ ትክክለኛ ውሳኔ እንድትወስኑ ይጠቅማቹሃል።

የጥገኝነት ማመልከቻ የምክር መመሪያ የሚለተሉትን ክፍሎች ያጠቃልላል።

ክፍል 1: ማይግራንት ሄልፕ አገልግሎቶች

እዚህ ክፍል ላይ ማይግራንት ሄልፕ ዩኬ ላሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ምን አገልግሎት እንደሚሰጥ እና እንዚህን አገልግሎቶች እንዴት ሊያገኙ እንደሚችሉ ያስረዳል።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 2: ጥገኝነት ስለ መጠየቅ

እዚህ ክፍል ላይ ዩኬ ውስጥ እንዴት ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚችሉ ማንበብ ይችላሉ።  እንዲሁም ደግሞ የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ከሆም ኦፊስ (ውስጣዊ ጉዳዮች) ጋር በሚያደርጉ ግዜ ምን እንደሚመስል እና በቃለ መጠይቁ ግዜ አንዳን አላግባብ ሁኔታዎች ነበሩ የሚሉ ከሆነ እንዴት ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ያስተያስረዳዎታል። በተጨማሪም ስለ ገንዘብ እና ቤት እርዳታ፣ ምን አይነት የጤና አገልግሎት ሊያገኙ እንደሚችሉ እና በቃለ መጠይቁ ግዜ ወይም ከጨረሱ ከጥቂት ግዜ በኋላ፣ ምን ወረቀቶች እንደሚሰጥዎት መረጃ ይሰጥዎታል። በየግዜው እየሄዱ ስለ ሚፈርሙበት ቀጠሮ እና የሕጋዊ አገልግሎት እንዴት ሊያገኙ እንደሚችሉ እንዲሁም ደግሞ ሁኔታዎ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሲኖር ለሆም ኦፊስ ማሳወቅ ስላለብዎት ግዴታ ያስረዳዎታል።

ሙሉውን የጥገኝነት ማመልከቻ አሰራር እዚህ ማየት ይችላሉ።

ስለ ጥገኝነት ማመልከቻ የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ አሰራር የሚያስረዳውን ቪድዮ እና በጥገኝነት ማመልከቻ ግዜ የሚሰጠውን እርዳታ እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ ይመልከቱ።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 3: ዋና የጥገኝነት ማመልከቻ ቃለ መጠይቅ

እዚህ ክፍል ላይ ስለ ጥገኝነት ማመልከቻ ዋና ቃለ መጠይቅ  እና ለቃለ መጠይቁ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ፣ እንዲሁም ደግሞ ከቃለ መጠይቁ በኋላ  ምን ውሳኔ ሊሰጥዎት እንደሚችል በተመለከተ አጠር ያለ መረጃ ያገኛሉ።

ስለ ጥገኝነት ማመልከቻ ዋና ቃለ መጠይቅ አሰራር የሚያስረዳውን ቪድዮ እዚ ይመልከቱ።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 4: ከውሳኔ በኋላፈቃድ ከተሰጥዎት

እዚህ ክፍል ላይ፣ የዩኬ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት በኋላ ስላለው ሁኔታ  እና ምን አይነት ወረቀቶች እንደሚሰጥዎት ያስረዳዎታል።  የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት በኋላ ማይግራንት ሄልፕ ምን አይነት እርዳታ ሊሰጥዎት እንደሚችል ይገልጻል።

የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት በኋላ ምን አይነት እርዳታ ሊያገኙ  እንደሚችሉ የሚያስረዳዎትን ቪድዮ ይመልከቱ።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 5: ከውሳኔ በኋላጉዳይዎን ካልተቀበሉት

እዚህ ክፍል ላይ ጉዳይዎን ካልተቀበሉት ስላለዎት አማራጮች፣ የሕጋዊ አገልግሎት እንዴት ሊያገኙ እንደሚችሉ እና ጉዳይዎን እንዴት ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ ያስረዳዎታል። ‘የይግባኝ መብትዎን ከጨረሱ’ ምን ማድረግ እንደሚችሉ፣ ማይግራንት ሄልፕ ምን አይነት እርዳታ ሊሰጥዎት እንደሚችልም ጭምር ያስረዳዎታል። በፈቃድዎ ወደ ሃገርዎ ስለ መመለስ አገልግሎትም ያስረዳዎታል።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 6: ልዩ  እርዳታ

ቤተሰብዎ ያሉበትን ቦታ የማያውቁ ከሆነ እንዴት አድርገው ማፈላለግ እንደሚችሉ እና የባርነት፣ ስቃይ፣ ግብረስጋዊ ጥቃት ወይም የሴት ልጅ ግርዛት ሰለባ ከነበሩ ምን እርዳታ ሊያገኙ እንደሚችሉ እዚህ ያገኛሉ። እንዲሁም ደግሞ ወንጀልን ለፖሊስ እንዴት መጠቆም እንደሚችሉ ያስረዳዎታል።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

ክፍል 7: ጠቃሚ አድራሻዎች

እዚህ ክፍል ላይ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች እርዳታ እና ድጋፍ የሚሰጡ የሌሎች ድርጅቶችን አድራሻ ያገኛሉ።

ሙሉውን ክፍል እዚህ ያንብቡ

 

ሙሉውን የጥገኝነት ማመልከቻ የምክር መመሪያ እዚህ ማንበብ ይችላሉ። 

 

የሚፈልጉትን መረጃ ካላገኙ፣ ምክር እና መመሪያ እንድንሰጥዎት በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን 0808 8010 503 ። አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ እናደርግልዎታለን። እንዲሁም ደግሞ ዌብ ቻት እና ኦን ላይን፣ በሚለተለው መንገድ የሚገኘውን የጥያቄ ፎርም መጠቀም ይችላሉ የአገልግሎት ተጠቃሚ መግቢያ  (ያግኙን የሚለውን ይጫኑ)። እንዲሁም ደግሞ የአገልግሎት ተጠቃሚ መግቢያ ላይ የሚገኘውን ማመልከቻ መሙላት እና መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

እባክዎን ያስተውሉ፣ መብትዎን በተመለከተ ምክር እና መመሪያ ልንሰጥዎት እንችላለን፣ ነገር ግን ሕጋዊ ምክር ወይም ሕጋዊ አገልግሎት ልንሰጥዎት አንችልም። እርዳታ ልንሰጥዎት ካልቻልን፣ ሕጋዊ አገልግሎት ሊሰጥዎት የሚችሉ የጠበቃዎች ዝርዝር እንሰጥዎታለን።