ምክር እና መመሪያ

የጥገኝነት ማመልከቻን ለመከታተል ከባድ እና የሚያደናግር ሊሆን እንደሚችል ይገባናል። ስለዚህ በየደረጃው ምን ማድረግ እንዳለብዎት ይሚያስረዳ መመሪያ አዘጋጅተንልዎታል። መብትዎን እና ያለብዎትን ሓላፊነት እንዲያውቁት እና ሁኔታዎን በአግባቡ ተረድተው የሚገባውን ውሳኔ እንዲያደርጉ ይረዳዎታል።

የጥገኝነት ማመልከቻ ምክር እና መመሪያ እነዚህ የሚከተሉትን ክፍሎች የሚያጠቃልል ነው።

ክፍል1: የጥገኝነት ማመልከቻ ማቅረብ

የጥገኝነት ማመልከቻ ማቅረብ እንዳለብዎት ለማወቅ እና የት ሄደው ማቅረብ እንዳለብዎት ለማወቅ፣ እርዳታም ደግሞ ከየት ሊያገኙ እንደሚችሉ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ። የጥገኝነት ማመልከቻ ስለ ማቅረብ ያለውን አሰራር እዚህ ሊያገኙ ይችላሉ።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 2: የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ

እዚ ክፍል ላይ ከሆም ኦፊስ (የአገር ውስጥ ጉዳይ) የሚኖርዎት የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ላይ ምን ሊያጋጥምዎት እንደሚችል እና ያለ አግባብ ነው ያስተናገዱኝ ብለው ካሰቡ እንዴት አድርገው ቅራኔዎን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ይገልጽልዎታል። እንዲሁም ደግሞ ስለ ገንዘብ እና የቤት እርዳታ፣ ስለ ሚፈቀድሎት የጤና እርዳታ፣ ቃለ መጠይቁ ላይ ወይም ከዚያ በኋላ ስለ ሚሰጥዎት ወረቀቶች መረጃ አለው። እየሄዱ ስለ ሚፈርሙበት ቀጠሮ፣ ስለ ሕጋዊ አገልግሎት እርዳታ እና ሁኔታዎ ላይ ለውጥ ካለ ለሆም ኦፊስ ማሳወቅ ስላለብዎት ሓላፊነትም መረጃ ይሰጥዎታል።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 3: ዋና ቃለ መጠይቅ

ስለ ዋና ቃለ መጠይቁ እና ለቃለ መጠይቁ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብዎት እና፣ ከዚያ በኋላም ምን እንደሚከተል አጠር ያለ መረጃ ይሰጥዎታል።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 4A: ከውሳኔ በኋላ – ከተቀበሉዎት

እዚህ ክፍል ላይ እንግሊዝ አገር የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት በኋላ ምን እንደሚከተል፣ ምን አይነት ወረቀት እንደሚሰጥዎት ያስረዳዎታል። ከዚያ በኋላም እዚህ አገር ለወደፊት ሕይወትዎ ለመዘጋጀት ስለ ሚያስፈልግዎት ነገር መረጃ ይሰጥዎታል -- ስለ ቤት፣ ስለ ስራ፣ ከመንግስት ስለ ሚሰጥ የገንዘብ እርዳታ፣ ስለ ኢንግሊሽ ትምሕርት እና ግዜው ሲደርስ ደግሞ የብሪቲሽ ዜግነት እንዴት ማመልከት እንዳለብዎት።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 4B: ከውሳኔ በኋላ  – ካልተቀበልዎት

እዚህ ክፍል ላይ ጉዳይዎን ካልተቀበሉት ምን ማድረግ እንዳለብዎት ስለሚኖርዎት አማራጮች ይገልጽልዎታል፣ ከጠበቃ ጋር ተገናኝተው እንዴት ይግባኝ ማለት እንዳለብዎት ይገልጽልዎታል። ‘ይግባኝ የሚሉበት እድል ካለቀ’ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እና በፍላጎትዎ ወደ አገርዎ ለመመለስ የሚፈልጉ ከሆነ ምን አይነት እርዳታ ለማግኘት እንደሚችሉ ይገልጽልዎታል።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 5: ሌላ መረጃ እና ልዩ የባለ ሙያ እርዳታ

እዚህ ክፍል ላይ ቤተሰብዎ የት እንዳሉ የማያውቁ ከሆነ ፈልጎ ስለሚያገናኝ እርዳታ፣ የባርነት ሰለባ ከሆኑ፣ ግፍ ከደረሰብዎ፣ የግብረ ስጋ ጥቃት ወይም ደግሞ የሴት ልጅ ግርዛት ሰለባ ከሆኑ ሊደረግልዎት የሚችለውን እርዳታ ይገልጽልዎታል። እንዲሁም ደግሞ የሆነ ወንጀል ከተፈጸመ ለፖሊስ እንዴት መንገር እንዳለብዎት ይገልጽልዎታል።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ክፍል 6: ጠቃሚ ቁጥሮች

እዚህ ክፍል ላይ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ለስደተኞች የተለያየ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶችን መረጃ ያገኛሉ።

ሙሉውን ክፍል ያንብቡት።

ሙሉውን መረጃ እዚ ላይ ሊያነብቡት ይችላሉ።

የሚያስፈልግዎትን እርዳታ ካላገኙ ምክር እና መመሪያ እንድንሰጥዎት በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይደውሉል 0808 8000 630  ወይም ደግሞ የጥገኝነት ማመልከቻዎ እስከ ሚታይ ድረስ እርዳታ እንዲጀምርልዎ ማመልከቻ ለማድረግ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉልን 0808 8000 631 በ 14 አይነት ቋንቋዎች እርዳታ የምንሰጥበት የአገልግሎት የስልክ መስመር አለን። ቋንቋዎትን ዝርዝሩ ላይ ካላገኙት እላይ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር ደውለው የትኛውን ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይንገሩ።

መብትዎን እና የሚገባዎትን እንዲያውቁ ምክር ልንሰጥዎት እንችላለን፣ የሕጋዊ አገልግሎት እና ሕጋዊ ውክልና ግን ልንሰጥዎት እንደነማንችል እንዲያስታውሱ እናሳስባለን። ልንረዳዎት የማንችል ከሆነ የባለሙያተኛ ጠበቃዎች ዝርዝር እንሰጥዎታለን።